የሳምንቱ ምንባብ፤ ምስባክና፤ ወንጌል
ምንባብ
ሮሜ ፲ ÷ ፩ – ፍፃሜ
፩ኛ ጴጥሮስ ፫ ÷ ፲፭ – ፍፃሜ
የሐዋርያት ሥራ ፩ ÷ ፩ – ፲፪
፩ኛ ጴጥሮስ ፫ ÷ ፲፭ – ፍፃሜ
የሐዋርያት ሥራ ፩ ÷ ፩ – ፲፪
ምስባክ
ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ።
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን።
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።
መዝ ፵፮÷፭ – ፮
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን።
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።
መዝ ፵፮÷፭ – ፮
ወንጌል
ሉቃስ ፳፬ ÷ ፵፭ – ፍፃሜ።
ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን
፩ኛ. ምስጢረ ጥምቀት
የማቴዎስ፡ወንጌል ፳፰፣፩፱ (28:19)
በአብ፣በወልድና፣በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው”
አዳም ከተፈጠረ በኋላ በዓርባ ፵ (40) ቀኑ ሔዋንም በሰማንያ ፹ (80) ቀኗ ወደ ገነት መግባታቸው በመመልከትና( ኩፋሌ ፬፣፱ (4፣9 ) እንዲሁም በብሉይ ላይ ደግሞ ሴት ልጅ ወንድ ስትወልድና ሴት ልጅ ስትወልድ ለወንዱ ጊዜ በዓርባ ፵ (40) ቀናት ለሴቷ ጊዜ በሰማንያ ፹ ( 80) ቀናት የመጽዳት ጊዜያት እንደምታሳልፍ ምሳሌ ሆኖ የኢትዮጵያ ተውኃዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ወንዶችን በዓርባ ፵ (40) ቀን ሴቶችን ደግሞ በሰማንያ ፹ ( 80)ቀን ወደቤተክርስቲያን መጥተው እንዲጠመቁ ታዛለች።



፪ኛ. ምስጢረ ሜሮን
ሜሮን ቃሉ ግሪክ ሲሆን ትርጉሙ ቅብዕ ማለት ነው።
ዮሐንስ ፪፣፳ (2፣20)
”እናንተስ ሁሉን ታውቁ ዘንድ ከመንፈስ ቅዱስ ቅብዐት ተቀብላችሗል”
የመንፈስ ቅዱስን ጸጋና በረከት ያሳድር ዘንድ ተጠማቂው በቅዱስ ዘይት ይታተማል።ይኽም ከጥምቀት ስነሥርዓት በኋላ ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ በጥምቀቱ ጊዜ ይፈጸማል።
፫ኛ. ምስጢረ ቁርባን
ዮሐንስ ፮፣፶፫-፶፱ (6:53-59)
”የወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ ሥጋን ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።…ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ”
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቁርባኑ ምዕመኑ የኃጢያት መደምሰሻ፣ የአጋንንት ድል መንሻ፣ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ኃይል ይቀበላል ብላ ታምናለች።
፬ኛ. ምስጢረ ክህነት
ዕብ ፮፣፳፮-፳፰ (6:26-28)
እውነተኛውን አማናዊውን ክህነት የመሠረተው ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ቅዱስ ተንኮልና ነውር፣ከኃጢያት የተለየ (ኃጢያት የለለበት) ከሰማያት ከፍ፣ከፍ ያለ እውነተኛ ሊቀ ካህናት ነው።”
ማቴ ፲፰፣፲፰
“በምድር የምታስሩት ኹሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድር የምትፈቱት ኹሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።”:
፭ኛ. ምሥጢረ ተክሊል
ማቴዎስ ፩፱፣፬-፮ (19 ቁ 4-6)
”ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው አለም፣ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር የተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ”
ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ሲሆን እርሱም በቤተሰብ ፈቃድና በሁለቱ በአንድ ወንድና በአንድ ሴት ሙሉ ስምምነትና ፈቃድ የሚፈጸም የቤተክርስቲያኒቱ ሥርዓት ነው። የሚፈጸመውም አንድ ጊዜ ብቻና በሥጋ ወደሙ ነው።
፮ኛ. ምስጢረ ንስሐ
”ነስሐ” ሲሆን በግዕዙ ንሥሐ ገባ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ ማለት ነው።
ማቴ ፬፣፩፯ (4፣17)
”መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ”
ሕዝ ፩፰፣ ፴-፴፪ (18፣30-32)
“ ንስሓ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋትም እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ፣የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ፣ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፣ የእስራኤል ቤት ሆይ ስለምን ትሞታላችሁ የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና ይላል ጌታ እግዚአብሔር ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ”
፯ኛ. ምስጢረ ቀንዲል
ዕብ ፭፣፲፫-፲፭ (5:13-15)
”ከእናንተ መከራ ያሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፣ደስ የሚለው ቢኖር እርሱ ይዘምር፣ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር እርሱ የቤተክርስቲያናትን ቀሳውስት ወደእርሱ ይጥራ፣ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት፣የዕምነት ጸሎት ድውዩን (በሽተኛውን) ያድናል፣ጌታም ያስነሳዋል፣ኃጢያትም ሠርቶ እንደሆነ ይሰረይለታል”
ለሥጋና ለነፍስም በሽተኛ የሚደረግ የጸሎትና የቀንዲል ቅባት ስነሥርዓት ነው። ታማሚ የሆኑ ምዕመናን ጸሎት ተደርጎላቸው ከበሽታቸው የሚድኑበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምታበረክተው መንፈሳዊ አገልግሎት ነው።